ስለ HUAWEI Cloud እና ግላዊነት መግለጫ

HUAWEI Cloud አየርላንድ ውስጥ በተደራጀው በ Huawei (ከአሁን በኋላ "እኛ" ወይም "የኛ" ተብሎ የሚገለጸው) አካል በሆነው Aspiegel Limited የሚቀርብ አገልግሎት ነው። HUAWEI Cloud አንዴ ከገቡ በኋላ ውሂብዎን በማንኛውም መሳሪያ መድረስ እና ማስተዳደር እንዲቻልዎ በራስ-ሰር የእርስዎን ውሂብ ክላውድ አገልጋዮች ጋር ያቀናጃል፣ መጠባበቂያ ያስቀምጣል እና ይጭናል።

ይህ መግለጫ የሚገልጸው፦

1. ስለ እርስዎ ምን አይነት ውሂብ እንሰበስባለን?

2. የእርስዎን ውሂብ የምንጠቀመው እንዴት ነው?

3. የእርስዎን ውሂብ የምናስቀምጠው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

4. የእርስዎን ውሂብ እናጋራለን?

5. የእርስዎ መብቶች እና አማራጮች ምንድን ናቸው?

6. እኛን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል?

7. ይህንን መግለጫ የምናዘምነው እንዴት ነው?


1 ስለ እርስዎ ምን አይነት ውሂብ እንሰበስባለን?

እንደ የ HUAWEI Cloud አገልግሎት አካል፣ የግል ውሂብዎን የምንሰበስበውና የምንጠቀመው በዚህ መግለጫ ውስጥ ለተጠቀሱት ዓላማዎች ብቻ ነው። የግል ውሂብ ማለት እኛ እርስዎን እንደ አንድ ተጠቃሚ ለይተን እንድናውቅዎት የሚያስችለን ማንኛውም መረጃ ማለት ነው። የግል ውሂብን ማሰናዳት ማለት በግል ውሂብ ወይም በግል የውሂብ ስብስቦች ላይ እንደ መሰብሰብ፣ መመዝገብ፣ ማደራጀት፣ ማዋቀር፣ ማከማቸት፣ ማስማማት ወይም መቀየር፣ ሰርስሮ ማውጣት፣ ማማከር፣ መጠቀም፣ በማስተላለፍ ይፋ ማድረግ፣ ማሰራጨት ወይም የሚገኝ ማድረግ፣ ማሰለፍ ወይም ማጣመር፣ መገደብ፣ መደምሰስ ወይም ማጥፋት ያለ ጨምሮ የሚከናወን በራስ-ሰር ሆነ አልሆነ ማንኛውም ክወና ወይም የክወናዎች ስብስብ ማለት ነው።

የሚከተለውን ውሂብ ሰብስበን እናሰናዳለን፦

የመለያ መረጃ፦ እንደ የመለያ ስም፣ ኢሜይል አድራሻ፣ የስልክ ቁጥር፣ መገለጫ ምስል፣ የተጠቃሚ ስም፣ የሀገር ኮድ፣ የመለያ መለያ፣ የተጠቃሚ የአገልግሎት ባጅ ያሉ።

የመሳሪያ መረጃ፦ እንደ መሳሪያ መታወቂያ (MEID፣ UDID ወይም IMEI እንደ የእርስዎ ስርዓት አይነት)፣ የመሳሪያ ሞዴል፣ ኦፐሬቲንግ ሲስተም፣ APK ስሪት፣ እና የቋንቋ ቅንብሮች።

የአውታረ መረብ መረጃ፦ እንደ የIP አድራሻ፣ አውታረ መረብ አይነት እና ግንኙነት ሁኔታ።

የአገልግሎት አጠቃቀም መረጃ፦ እንደ የ HUAWEI Cloud ስሪት፣ የማውረጃ ምንጭ፣ መተግበሪያ የተከፈተበት እና የተዘጋበት ሠዓት፣ የተጫኑ መተግበሪያዎች ዝርዝር፣ ክሊኮች እና ተጋላጭነት፣ የጥቅል መረጃ (ስም፣ መጠን እና የቆይታ ጊዜ)፣ የግዢ መረጃ (ሠዓት፣ መጠን እና የማዘዣ መታወቂያ)፣ የስርዓት መዝገቦች እና የብልሽት መዝገቦች።

የተቀናጀ፣ መጠባበቂያ የተቀመጠ፣ በራስሰር-የተጫነ ውሂብ (ውጤቶች እንደ ተመዘገቡበት የ HUAWEI መታወቂያ አገር/ክልል ሊለያይ ይችላል)፦ እንደ የተቀናጀ ውሂብ (እነ እውቅያዎች፣ የቀን መቁጠሪያ ሁነቶች፣ የ Wi-Fi ቅንብሮች፣ ማስታወሻዎች፣ የሥነ ጥበብ ማዕከልን ጨምሮ)፣ የ Cloud ባክአፕ ውሂብ (እነ እውቅያዎች፣ የቀን መቁጠሪያ ሁነቶች፣ የ Wi-Fi ቅንብሮች፣ ማስታወሻዎች፣ የሥነ ጥበብ ማዕከል፣ ቅጂዎች፣ የታገዱ ዝርዝሮች፣ የጥሪ ቅጂዎች፣ የሰዓት ቅንብሮች (ማንቂያ እና የፈለጉት ከተማዎች)፣ የስልክ አስተዳዳሪ ቅንብሮች፣ መልዕክት (SMS፣ MMS)፣ የአሳሽ እልባት/የመረጃ ፍሰት፣ የአየር ሁኔታ ቅንብሮች፣ የ SmartCare ቅንብሮች፣ የ ዴስክቶፕ አቀማመጥ፣ የ ካሜራ ቅንብሮች፣ የ ስርዓት ቅንብሮች፣ ኤፍ ኤም ሬዲዮ፣ የ HiCare ቅንብሮች፣ ልጣፍ፣ የተጫኑ የመተግበሪያዎች APK፣ ሙዚቃ) እና የ Huawei Drive ፋይሎች (ማንኛውም ለመጫን የመረጡት የውስጥ ፋይሎችን ጨምሮ)፣ በ ራስሰር የተጫነ ውሂብ (ቅጂዎች እና የታገዱ ዝርዝርን ጨምሮ)።


ውሂብዎን ለማስተዳደር በእርስዎ የ HUAWEI መታወቂያ ወደ ኦፊሴላዊው የHUAWEI Cloud ድህረ ገፅ (cloud.huawei.com) ከገቡ፣ የሚከተለው መረጃም ይሰበሰባል፦

የአሳሽ እና የአጠቃቀም መረጃ፦ እንደ ኩኪስ፣ የIP አድራሻ፣ የ አሳሽ አይነት፣ የጊዜ ክልል፣ ቋንቋ፣ እና የማውስ እና የ ኪቦርድ ክንዋኔ። ኩኪስ ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎን የኛን የኪኪስ ፖሊሲ ያንብቡ።

ማሰናዳት የሚያካትተው የማሰናዳቱን አላማ የሚያሟላ የግል ውሂብን ብቻ ነው። የተሰናዳ የግል ውሂብ ይዘቶች እና ወሰን ከተገለጸው የመሰናዳት ዓላማዎች ጋር የሚጎዳኝ ነው እናም ከመሰናዳታቸው ዓላማ አንጻር ከልክ ያለፈ ሊሆን አይችልም።

HUAWEI Cloud የማቀናጀት እና መጠባበቂያ የማስቀመጥ አገልግሎትን ማቅረብ እንዲችል የመሳሪያ መረጃን ለማግኘት እና ማከማቻ፣ ካሜራ፣ SMS፣ እውቅያዎች እና የቀን መቁጠሪያን ለመድረስ ስልኩን መድረስ ያስፈልገዋል።

2 የእርስዎን ውሂብ የምንጠቀመው እንዴት ነው?

የግል ውሂብ የሚሰናዳው ህጋዊ እና ፍትሀዊ በሆነ መልኩ በተጠቀሰው፣ ቅድሚያ በተቀመጠው እና በሕጋዊ ዓላማዎች ነው። የግል ውሂብ የሚሰናዳው የሚመለከተው ህጋዊ መሠረት ሲኖር ብቻ ነው። የ HUAWEI Cloud ን ክንውኖች ለመዘርጋት፣ እነ Cloud ማቀናጀት፣ Cloud ባክአፕ፣ Huawei Drive እና ሌሎች የውሂብ አገልግሎቶችን ጨምሮ፣ እንዲሁም ኮንትራታዊ ግዴታዎችን ለማሟላት፣ መተግበሪያው ለደንበኛ ግንኙነት አስተዳደር፣ ለድጋፍ እና ግንኙነት፣ ለደንበኛ ቅሬታ አያያዝ፣ ለጥገና፣ ለሶፍትዌር እና የስርዓት ዝማኔዎች፣ ለተጠቃሚ መለያ እና ለምርመራ እና ጥገና አላማዎች የእርስዎን ውሂብ መሰብሰብ እና ማሰናዳት ያስፈልገዋል።

በተጨማሪም፣ በህጋዊ ፍላጎቶች መሰረት የእርስዎን የግል ውሂብ ለሚከተሉት አላማዎች እንጠቀማለን፦

ለ ስታትስቲክስ እና ምርት ማሻሻያ አላማዎች፣ በእርስዎ የአጠቃቀም እንቅስቃሴ ላይ በመመስረት የተጠቃለሉ ቡድኖችን መፍጠርን ጨምሮ። ይህ የተጠቃሚዎቻችንን ፍላጎቶች እንድንረዳ እና የአሁንና የወደፊት የአገልግሎቶቻችንና የአቅርቦታችንን ጥራት እና የተጠቃሚ ተሞክሮ እንድናሻሽል ያስችለናል። ከታች አንቀጽ 5.6 ላይ እንደተገለጸው እንደዚህ ያለውን ማሰናዳት መቃወም ይችላሉ።

ለገበያ ዓላማዎች፣ ስለ የኛ አቅርቦት፣ የሽያጭ ማስተዋወቂያ እና ሌሎች የገበያ አላማዎችን ጨምሮ ግንኙነት ለማረግ፣ እንዲሁም ገበያን ለማስፋፋት የተጠቃለሉ የታለሙ ቡድኖችን ለመፍጠር። የደንበኞችን ምርጫዎች ማወቅ አቅርቦታችን እንድናነጣጥር እና የደንበኞቻችን ፍላጎቶችና ምኞቶች በተሻለ የሚያሟሉ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን እንድናቀርብ ያስችለናል። ከታች አንቀጽ 5.6 ላይ እንደተገለጸው እንደዚህ ያለውን ማሰናዳት መቃወም ይችላሉ።

የመረጃ ደህንነት ዓላማዎች፣ ደህንነታቸው የተጠበቁ እና አስተማማኝ አገልግሎቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ የተለያዩ ዓይነቶች የአገልግሎቶችን ያለአግባብ መጠቀም እና ማታለሎችን ማወቅ ወይም መከላከልን ጨምሮ።

በተጨማሪ የምናሰናዳው ለግብር እና ለሒሳብ ዓላማዎች ሲባል እኛን በሚመለከቱ ህጎች እና ደንቦች መሠረት የእርስዎን የጥቅል መረጃ (ስም፣ አቅም እና ጊዜ)፣ የግዢ ሰዓት፣ የትዕዛዝ መታወቂያ ናቸው።

የግል ውሂብ ከህገወጥ ወይም ካልታሰበ መዳረሻ፣ ከመደምሰስ፣ ከመቀየር፣ ከመታገድ፣ ከመቀዳት፣ ለሌላ ከመቅረብ እና ከመሰራጨትና እንዲሁም የግል ውሂቡን በተመለከተ ከሌሎች ህገወጥ እርምጃዎች ለመከላከል በስጋቶች ላይ የተመሠረቱ አስፈላጊዎቹን ህጋዊ፣ ድርጅታዊ እና ቴክኒካዊ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ እናረጋግጣለን።

ራስሰር በሆነ የተደራጀ የውሂብ ጎታ አስተዳደር ስርዓቶችን በመጠቀም እንደዚሁም በሌሎች ሶፍትዌር እና ሃርድዌርን በመጠቀም የእርስዎን የግል ውሂብ እንድናሰናዳ ይስማማሉ እና ፍቃድዎን ይሰጡናል።

3 የእርስዎን ውሂብ የምናስቀምጠው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

የእርስዎን የግል ውሂብ የምናስቀምጠው በዚህ መግለጫ ውስጥ ለተጠቀሱት ዓላማዎች አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ ነው።

የእርስዎ ውሂብ የደንበኛ ግንኙነቱ እስከሚቆይበት ጊዜ ድረስ እናሰናዳለን እና እናስቀምጣለን። HUAWEI Cloud ን መጠቀም ለ አስራ ሁለት (12) ወራቶች ሲያቆሙ፣ ውሂብዎ ይጠፋል። ስለ መጥፋቱ አስቀድመን በተገቢው መንገድ፣ ለምሳሌ በኢሜይል እናሳውቆታለን። የእርስዎን የ HUAWEI መታወቂያ መለያ ሲሰርዙ ከእርስዎ መለያ ጋር የተዛመደ የግል ውሂብ እና እንደ HUAWEI Cloud ያሉ ተጓዳኝ አገልግሎቶች ይደመሰሳሉ። ሆኖም ግን፣ የሚከተሉትን እናቆያለን፦

የ HUAWEI Cloud ጥቅል መረጃ (ስም፣ አቅም እና የቆይታ ጊዜ)፣ የግዢ መረጃ (ሠዓት፣ መጠን እና የማዘዣ መጣወቂያ) ዝውውሩ ከተፈጸመበት አንስቶ እስከ ሰባት (7) ወር።

ለደንበኛ ግንኙነት አስተዳደር የተሰናዳ የግል ውሂብ እንደ ቅሬታዎች፣ የውሂብ ጉዳይ ጥያቄዎች እና የውል አስተዳደር ዓላማዎች የ HUAWEI መታወቂያ መለያዎ ከተሰረዘ በኋላ እስከ አምስት (5) ዓመታት፤ ለትንታኔ እና ግንባታና እንዲሁም ለሽያጭ ማስተዋወቅ እና የገበያ ዓላማዎች ጥቅም ላይ የሚውል ውሂብ ከተሰበሰበበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አስራ ሁለት (12) ወራት፣ እንዲህ ያለ መሰናዳት ካልተቃወሙ በስተቀር።

የእርስዎን ውሂብ እና አገልግሎቶች ደህንነት ለማረጋገጥ የሚሰናዱ መጠባበቂያዎች እና የመተግበሪያ መዝገቦች፣ ከተፈጠሩበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት (6) ወራት።

የእንቅስቃሴ መዝገቦች እና የስርዓት መዝገቦች የሚመለከተው ስታቲስቲካዊ ትንተና ሲጠናቀቅ ወዲያውኑ ይሰረዛሉ፤ የስህተት መዝገቦች መረጃው ከተሰበሰበ ከሰባት (7) ቀናት በኋላ በራስ-ሰር ይሰረዛሉ።

የማቆያ ጊዜው ሲያበቃ በሚመለከታቸው ህጎችና ደንቦች እስካልተጠየቀ ድረስ የግል ውሂብዎን እንሰርዛለን ወይም ስም አልባ እናደርገዋለን።

4 የእርስዎን ውሂብ እናጋራለን?

የእርስዎን ውሂብ ሩሲያ ባሉ የውሂብ ማዕከሎች እናከማቻለን። ከሩሲያ ፌደሬሽን ወደ ሌሎች ሀገሮች እንደ አየርላንድ እና ፊንላንድ ያሉ እና ከ አህ/ኢኢኤ እና ሩሲያ ፌደሬሽን ውጭ የሆኑ ሌሎች አገራት ላይ የግል ውሂብዎን የድንበር ተሻጋሪ ዝውውር ልናከናውን እንችላለን። እኛ የግል ውሂብዎን ወደ ከሩሲያ ፌዴሬሽን ውጭ የሆኑ ሀገራት ድንበር አሻግረን እንድናስተላልፍ በሩሲያ ፌዴሬሽን ህግ መሠረት የሚያስፈልገው ፈቃድዎን ሰጥተዋል።

የእርስዎን ውሂብ የምናጋራው፦

በሚመለከተው ህግ መሠረት ወይም ከህጋዊ ሂደት ጋር በተያያዘ ለህጋዊ ሂደት ስልጣን ካለው አካል ለመጣ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሲያስፈልግ።

እንደ የውህደት፣ ግዢ፣ የእሴቶች ሽያጭ (እንደ የአገልግሎት ስምምነቶች) ወይም እንደ የአገልግሎት ወደ Huawei ቡድን ህጋዊ አካል ወይም ሌላ ኩባንያ ሽግግር አካል ሲያስፈልግ።

5 የእርስዎ መብቶች እና አማራጮች ምንድን ናቸው?

የሚከተሉት መብቶች እና አማራጮች አለዎት፦

5.1 ውሂብዎን መድረስ


መሳሪያዎ ላይ ወደ ቅንብሮች > HUAWEI መታወቂያ > ቅንብሮች > ውሂብዎን ይጠይቁ በመሄድ ስለ እርስዎ በ HUAWEI Cloud ውስጥ ሰብስበን ያስቀመጥነው የግል ውሂብን መረጃ ወይም ቅጂ መጠየቅ ይችላሉ።

እንዲሁም እርስዎ ያቀናጁትን፣ መጠባበቂያ ያስቀመጡለትን ወይም የጫኑትን ውሂብ ከ HUAWEI Cloud መተግበሪያ ወይም ኦፊሴላዊ ድህረ ገፅ (cloud.huawei.com) ላይ መድረስ ወይም ማውረድ ይችላሉ።

ለተጨማሪ የመድረስ ጥያቄ፣ እባክዎን ያነጋግሩን።


5.2 ውሂብዎን ማስተካከል


ውሂብዎን ወቃትዊ እና ትክክለኛ እንደሆነ ለማቆየት በመሳሪያዎ ላይ ወደ ቅንብሮች > HUAWEI መታወቂያ በመሄድ ውሂብዎን መድረስ እና ማስተካከል ይችላሉ።

እርስዎ ያቀናጁትን፣ መጠባበቂያ ያስቀመጡለትን ወይም የጫኑትን ውሂብ ከ HUAWEI Cloud መተግበሪያ ወይም ኦፊሴላዊ ድህረ ገፅ (cloud.huawei.com) ላይ መድረስ እና መቀየር ይችላሉ።


5.3 ውሂብዎን ማዛወር


በመሳሪያዎ ላይ ወደ ቅንብሮች > HUAWEI መታወቂያ> ቅንብሮች > ውሂብዎን ይጠይቁ በመሄድ በ HUAWEI Cloud ውስጥ ለእኛ ያቀረቡትን የግል ውሂብ በተለምዶ ስራ ላይ በሚውል እና ሊነበብ ወደሚችል ቅርጸት ማዛወር ይችላሉ።


እንዲሁም እርስዎ ያቀናጁትን፣ መጠባበቂያ ያስቀመጡለትን ወይም የጫኑትን ውሂብ ከ HUAWEI Cloud መተግበሪያ ወይም ኦፊሴላዊ ድህረ ገፅ (cloud.huawei.com) ላይ ማውረድ ይችላሉ።


5.4 ውሂብዎን ማጥፋት

እርስዎ በማንኛውም ጊዜ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦

የእርስዎን የተቀናጁ፣ መጠባበቂያ የተቀመጠላቸው እና ሌሎች የውሂብ ዓይነቶች ከመሳሪያዎ ላይ በማጥፋት ማጥፋት ይችላሉ። ያጠፉት በራስ-ሰር ከክላውድ ጋር ይቀናጅ እና ይዘመናል።

የተከማቸውን ውሂብዎን በቀጥታ ከ Huawei Drive ላይ በማጥፋት ማጥፋት ይችላሉ።

እውቅያዎች፣ የሥነ ጥበብ ማዕከል፣ ቅጂዎችን፣ የታገዱ ዝርዝሮችን እና Huawei Drive ፋይሎችን ጨምሮ ውሂብዎን ለማጥፋት ወደ ኦፊሴላዊው HUAWEI Cloud ድህረ ገፅ (cloud.huawei.com) ይግቡ።

የእርስዎን HUAWEI መታወቂያ ማጥፋት። ይህ በ HUAWEI Cloud ውስጥ ያለውን የግል ውሂብዎን ጨምሮ ከእርስዎ የHUAWEI መታወቂያ ጋር የተዛመደውን የግል ውሂብዎን ይደመስሳል።

አንቀጽ 5.6 ላይ እንደተገለጸው የግል ውሂብዎን ማሰናዳት መቃወም። ተቃውሞዎ ትክክለኛ ከሆነ እና ማሰናዳቱን ለመቀጠል ሕጋዊ መሰረት የማይኖረን ከሆነ በእርስዎ ሕጋዊ ተቃውም ወሰን ውስጥ የሚወድቀውን ውሂብ እንደመስሳለን።

የእርስዎን የግል ውሂብ ማሰናዳት ሕጋዊ አይደለም ብለው የሚያስቡ ከሆነ ያግኙን እና ውሂብዎ ይደመሰሳል።

ከላይ በገለጹት ድርጊቶች እና በማቆያ ጊዜዎች አንቀጽ 3 ላይ በተገለጸው መሰረት ሳንዘገይ አስፈላፊ ሲሆን የግል ውሂብዎን እንደመስሳለን ወይም ስም አልባ እናደርጋለን።

5.5 የመቃወም መብት

የእርስዎን ውሂብ ለስታቲስቲካል፣ ምርት ማሻሻል ወይም ሽያጭ እና ገበያ ማስፋፋት አላማዎች መሰናዳታቸውን መቃወም ከፈለጉ፣ እባክዎን ያነጋግሩን።

ጥያቄውን ሲያቀርቡ እባክዎ የጥያቄውን ወሰን ይግለጹና በእርስዎ የ HUAWEI መታወቂያ ወደ HUAWEI Cloud ለመግባት የሚጠቀሙበትን የእርስዎን ኢሜይል አድራሻ ወይም የስልክ ቁጥር ይስጡን።

ባቀረቡት ጥያቄ ለመቀጠል የእርስዎን ማንነት ለማረጋገጥ እናነጋግረዎታለን።

5.6 ማሰናዳትን መገደብ

የእርስዎን የግል ውሂብ ማሰናዳትን መገደብ ከፈለጉ፣ እባክዎን ያነጋግሩን። በሚከተሉት ሁኔታዎች ስር የእርስዎን ውሂብ መሰናዳት የመገደብ መብት አለዎት፦

ውሂብዎ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ተሰናድቷል፣ ነገር ግን መደምሰስ አይፈልጉም።

ሊመሰርቱት፣ ሊጠቀሙት እና ሊከላከሉት የሚያስፈልገዎት እና ውሂብዎን ሳንጠብቅ ስንቀር እንድንጠብቀው ሊጠይቁን የሚችሉት ህጋዊ የይገባኛል ጥያቄ አለዎት።

የተቃውሞ ጥያቄዎ የእኛን ማረጋገጥ በመጠባበቅ ላይ ነው።

ጥያቄውን ሲያቀርቡ እባክዎ የጥያቄውን ወሰን እና የጥያቄው መሠረት ይግለጹ፣ እና ወደ እርስዎ HUAWEI Cloud ለመግባት የሚጠቀሙበትን የእርስዎን ኢሜይል አድራሻ ወይም የስልክ ቁጥር ይስጡን።

ባቀረቡት ጥያቄ ለመቀጠል የእርስዎን ማንነት ለማረጋገጥ እናነጋግረዎታለን።

6 እኛን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል?

በ አንቀጽ 5 ውስጥ የእርስዎን የውሂብ መቃወም መብቶች እንዴት እንደምትጠቀሙባቸው ምክር ማግኘት ይችላሉ። በእርስዎ የውሂብ መቃወም መብቶች ላይ ወይም በእኛ የእርስዎን የግል ውሂብ ማሰናዳት ላይ ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች ወይም ጥቆማዎች ካለዎት፣ እባክዎን ያነጋሩን።

እኛ፣ አስፒጀል ሃላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት፣ ውሂብ ተቆጣጣሪዎች ነን። የዋና መስሪያ ቤታችን አድራሻ፦ Aspiegel Limited, First Floor, Simmonscourt House, Simmonscourt Road, Dublin 4, D04 W9H6, Ireland. የምዝገባ ቁጥር 561134።

የእኛ የውሂብ ጥበቃ ባለሞያ እውቂያ ዝርዝር፦ dpo@huawei.com።

በዚህ መግለጫ ወይም ተግባራዊ በሚደረጉት የውሂብ ጥበቃ ሕጎች መሰረት እኛ የእርስዎን የግል ውሂብ አናሰናዳም ብለው የሚያስቡ ከሆነ፣ የእርስዎ የውሂብ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር ወይም አየርላንድ ውስጥ ያለ የውሂብ ኮሚሽነር ጋር ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። የመሟገት መብት፣ የጉዳት ካሣ ጥየቃ እና/ወይም በሕግ የሞራል ካሣ ጨምሮ መብቶችዎን ለማስጠበቅ በተገቢው ሕግ ተቀባይነት ያላቸውን እርምጃዎችን የመውሰድ መብቶች አለዎት።

7 ይህንን መግለጫ የምናዘምነው እንዴት ነው?

ከጊዜ ወደ ጊዜ ልንቀይረው ስለምንችል የዚህ መግለጫ የመጨረሻ ስሪት እንዳለ በየጊዜው ከመተግበሪያው ቅንብሮች ላይ እንዲፈትሹ እናበረታታዎታለን። በዚህ መግለጫ ላይ ቁሳዊ ለውጥ ካደረግን፣ በለውጡ ተፈጥሮ ላይ በመመስረት እንደ የማሳወቂያ የንግግር ሳጥን፣ በመሳሪያዎ ላይ የማሳወቂያ መልዕክት፣ ኢሜይል፣ ወዘተ ያሉትን ጨምሮ ተገቢ የሆነ መንገድ በመጠቀም እናሳውቀዎታለን።

የቅርብ ጊዜ ስሪት፦ ኖቬምበር 30, 2018